ሁኚ ንግስት በቤታችን
አድርጊልን እርስት ፍቅርሽን
ቅድስት ድንግል እዘኝልን
ሙይልን በረከት ቤታችን
ነሽና ንግስት
አ የአምላክ እናት
የአንቺን ፍልሰት
ያዚሙ መላእክት
የሰላም ንግስት
በልጅሽ መንግስት
አምጪ ስምምነት
በክርስቲያን ህብረት
ነሽና ንግስት
ለተጨነቁት
ከንስሐ ቤት
አውጫቸው ከእሳት
የሐዘን እናት
ከልጅሽ መስዋት
አሰጭን ምህረት
ነፍሴን አድኛት
ላምልክህ እንጂ በሁሉም ምክንያት አሃ(2)
ኧረ እኔ አልችልም ስኬቴን ማስላት
ዘምሬ አልቆምም ኑሮን በማስላት
ዛሬም እልሃለሁ ተባረክ ኧ (2)
ተባረክ አምላኬ ብሩክ ነህ ተባረክ
ጠላት ይፈር ይስማ ተባረክ ኧ ተባረክ
ጌታዬ ብሩክ ነህ ተባረክ
አምልኮዬን ይኽው ተባረክ ኧ ተባረክ
አምላኬ ብሩክ ነህ ተባረክ
ምስጋና የሚሰዋ ያከብረኛል እንዳልከው
በቅዱስ ቃልህ እንደተናገርከው
ስዘምር ልኑርልህ ብዙ ክብር አለኝ እኮ
ሁኔታን (ምክንያትን) አልጠብቅም ለአምልኮ (2)
ተባረክ እግዚአብሔር ተባረክ
ተባረክ በአለም ዝናህ ይተረክ
ተመለክ ንጉሴ ተመለክ
ተመለክ ማምለኬን ከወደድክ
ባለግርማ (3) ባለሞገስ
ባለሞገስ (2) ነህ ስምህ ይወደስ
ሲሞላልኝ ዘምሬ ደስታዬ ጥግ ደርሶ
በራድ ስሜት አይደለም መልሶ
ፍፁም ያልተነካካ ከሁኔታዬ ጋራ
ልዩ ምስጋና ይፍሰስ በስፍራህ (2)
ቀስቃሼ እኮ እሱ አይደለም ባህር ቀድሞ ተከፍሎ
ለምስጋና የሚያስነሳኝ ቀጥሎ
ወጀቡ እያለ ፊቴ ጌታ አንተ ነህ ምክንያቴ
አምልኮዬን አይለካም ስኬቴ (2)
ምን ያህል ጥልቅ ነው ለእኔ ያለህ ፍቅር
ነፍስን የሚያሰጥ ዋጋን የሚያስከፍል
ኦ ኢየሱስ /4x/
እንዲህ የወደድከኝ ፍቅር የሚገባኝ
ኧረ እኔ ማነኝ /2x/
ሆኜ ሳለሁ የአንተ አሳዳጅ
ጠላት እንጂ አይደል ወዳጅ
በፍቅርህ የገዛኸኝ ለመሆኑ እኔ ማነኝ
እራሴን ሳውቀው ማንነቴ
የበዛ ነው ኃጢአቴ /2x/
እንዲህ የወደድከኝ ፍቅር የሚገባኝ
ኧረ እኔ ማነኝ /2x/
ይደንቀኛል ሁልጊዜ
የአንተስ ፍቅር ኢየሱሴ
እስከሞት ድረስ ወደኸኛል
እራስህን ሰጥተህ አድነኸኛል
ከአእምሮዬ በላይ ነው
የአንተን ፍቅር አልገልጸው /2X/
ምን ያህል ጥልቅ ነው ለእኔ ያለህ ፍቅር
ነፍስን የሚያሰጥ ዋጋን የሚያስከፍል
ከምን ጋራ ላወዳድረው
ጌታ ፍቅርህ ወደር የለው
የፍቅር ጥግ መጨረሻው
በአንተ ታየ መደምደሚያው
ከዚህም በላይ ፍቅር የለም
ደግሞ አይታይ ለዘላለም /2X/
ኦ ኢየሱስ /4x/
እንዲህ የወደድከኝ ፍቅር የሚገባኝ
ኧረ እኔ ማነኝ /2x/
ሰው አስተውል ረጋ ብለህ ከንቱ
ሩጫህን ገታ አድርገህ
አስቀድመህ ፅድቁን ብትሻው
ይጨመራል ሌላው ሌላው
1. ስለምድር ብቻ አጥብቀው ቢለፉ
ምንም ውጤት የለው ድካም እንጂ ትርፉ
እጅግ ለሚበልጠው ለሰማዩ እርስትህ አብዝተህ
ብትለፋ ያነው የሚጠቅምህ
2.የሚያስፈልገንን አስቀድሞ ያውቃል
እግዚአብሔር ጨክኖ መች እረስቶህ ያውቃል
ከሌሎች ፍጥረታት ይልቅ አሰበልጦ
እግዚአብሔር ያስባል ስለ እኛ ተገዶ
3.የሰው ዓይን ከማየት ፈጽሞ አይጠግብም
ጆሮህም ከመስማት ከቶውንም አይሞላም
የሰው ልጅ ፍላጎት ወሰን የሌለው ነው
የእግዚአብሔር ጽድቅ ግን እርሱ እርካት ነው
ባወቅሁ መጠን ጌታዬ ወደድኩህ
ባወቅሁ መጠን በፍቅር ወደድኩህ
ባመንኩህ መጠን እረፍቴን አበዛህ
ባመንኩህ መጠን ህይወቴን አረጋጋሁብህ
ስላመድህ ቀርበኸኝ በፍቅር
ጠርተኸኝ በፍቅርህ በቤትህ
ለካ እንዲህ ነህ አልኩህ /2
ጌታ ተረዳሁልህ
ንፁህ ልቤ ምንግዜም ቢወድህ
አምላኬ ቢያደንቅህ ቢያውቅህ
ነገም ያምናል አዲስ ነህ /2
ከመታወቅ በላይ ነህ
ከህይወቴ ሸክሜን ስታነሳ
ሳይህ ስታነሳሳ
ኢየሱስ ሆንከኝ ማትረሳ
ለእኔ ሆንከኝ ማይረሳ
አይኔን ከአንተ ላላነሳ
አልለወጥ ያለኝ ሕይወቴ
መነካት ያለበት ዘመኔ
ላንተ የማይመች ጓዳዬ
መከፈል ያለበት እዳዬ
እልፍ ቢሆን መጣሁ ወዳንተ
ሰላም አለህና ጌታዬ
1. በመብራትህ ብርሃን ብመራም
ስፈተን ስምህን ብጠራም
እረኛዬ ኢየሱስ ከፊቴ
ወደዋለሁ ይህ ልጅነቴ
ስደክም የማትደክም
ማትርቀኝ እኔ ስርቅህ
ብቻህን ወዳጅ ነህና
ሌላው እንኳን በቀረብኝ
2. በልጦብኝ ካፈሰስከው ደም
የሚያስረኝ ዙርያዬ የለም
ሁንልኝ የልቤ ንጉስ
እንደወደድከኝ ልመላለስ
በድካሜ የማትጥለኝ
መንፈስህ መቼ ተለየኝ
እወድህ ዘንድ እንደገና
በፀጋህ ገና አለሁና
አልለወጥ ያለኝ---
ስደክም የማትደክም
1. ካላገኝሁት ነገር
ቀረኝ ከምለው ቁም ነገር
ያረክልኝ ስለበዛ
አምላኬ ላመልክህ መጣው ከዛ
ከነፍሴ ፈሶ በፊትህ
ዙፋንህ ይክበር መቅደስህ
በውስጤ ያለው ይኼ ነው
ሁልጊዜ አመሰግናለው
አመሰግንሃለው/8/
2.በጨለማ አለም ገብቼ
እንዳልቀር ልጅህ ጠፍቼ
በኢየሱስ ለእኔ ደርሰሃል
ሕይወቴን ከሞት ታድገሃል
በአንተ ካፈረ ከሳሼ
ዝምታ ሳይሆን ምላሼ
በምስጋናዬ መጣሁ
መች ዝዬ አቋርጣለሁ
3.በሕይወት ላኖረኝ ትእግስትህ
ስለ ዘወትር ጥበቃህ
አቤቱ ስለ ውለታህ
ስለማይነገር ስጦታህ
ሳልሳሳ ላብዛ ምስጋና
ሌላ የምልህ የለምና
አሜን ይድረስህ ወደደዉ
አምላኬ ለክብርህ ስቀኘሁ
አተወኝም አትረሳኝምና አባቴ ላትለቃት ቃል ገብተሀል ለህይወቴ
ያላንተማ መች ይሆንላታል ነፍሴ
ያከበርካት አንተ ነህና የሱሴ
1. ደካማ ነኝ ከሌለኸኝ ብርቱ ነኝ ስታየኝ
ለሰንኮንዷም ብትሆን ያለ አንተ ጠፊ ነኝ
በምረትህ ብቻ ነው የበሩት አይኖቼ
ፀንቼም የቆምኩት ይዘኸኝ እግሮቼ
አልርቅም ከመንገድህ ኖራለሁ ቤትህ
በረከት ሰላሜ ነህ አምንሀለው
ያንተን ቸርነት አይቻለው
የህይወት መንገዴ ነህ አምንሀለው
2. ጥበቃህን አይቶ ለተደገፈብህ
ትሸፍነዋለህ ከልለህ በደምህ
ወጥመድ አያገኘው እርምጃው ተቃንቷል
ልቡም አይናወጥ በክንድህ ላይ አርፏል
ይህንን የምለው አንተ የኔ
የሚቆም ለዘላለም ሆኖ ጎኔ
ያንተን ቸርነት አይቻለው
የህይወት መንገዴ ነህ ወድሀለው
ስምህ ይጣፍጠኛል አንደበቴን ሳወራ ስናገረው
ባይኖችህ መታየቴኮ ጌታ ከሰው አእምሮ በላይ ነው
ታይቻለው ተጎብኝቼ በአንተ እረፍቴንም ሁሉ አጊንቼ
ታይቻለው ተጎብኝቼ ባንተ ሀሴትን ሁሉ አጊንቼ
አመሰግንሀለው /4/
አይዞህ በለኝ አትለኝ ጌታዬ ሆይ በጉዞዬ
እንድራመድ በመንገድህ ፈለግህን ተከትዬ/2/
1. መንፈስህን አፍስስልኝ እንዲያጽናናኝ
ቃልህ ደግሞ የጉዞ ስንቅ ይሁንልኝ
መስቀልህን ለመሸከም እለት እለት
ምርኩዝ ሁንልኝ ጌታ ሆይ ልመራበት /2/
2. ከውድቀቴ እንድነሳ ዘይትህን ቀባኝ
ብርታት ሆኖኝ ወደ ጽዮን እንዲያደርሰኝ
አንተን ይዤ እንድራመድ በዚች ምድር
ለመቀበል የድል ችቦ ከጽዮን አገር
3. ሄጄ ሄጄ መሃል መንገድ እንዳይደክመኝ
ዳዴ በለኝ ጌታዬ ሆይ እንዳትለቀኝ
አንድ ብዬ ጀምሬአለሁ ይህ ጉዞዬን
አሳምርልኝ ጌታ ሆይ መጨረሻዬን
ኢየሱስ የእኔ ሰላሜ
ኢየሱስ የእኔ ዕረፍቴ
ቁስል ሕመሜን ፈዋሼ
የሐዘኔ አጽናኝ ፈዋሼ
አንተ ነህ ሰላሜ የእኔ
አንተው ነህ ደስታዬ ዛሬ
አንተ ነህ ዕረፍቴ የእኔ
አንተው ነህ ማዕረጌ ዛሬ
1.በሌላ አይደለም ዛሬ እኔ ዕፎይ የምለው
ከላይ ከታች የለኝ ደግሞ የምደረድረው
አንተን ብቻ ሳስብ ደስ ደስ ይለኛል
ኢየሱሴ እንኳን ሰላም ይሰማኛል
አንተ ነህ ሰላሜ የእኔ…..
2. የረሃቤ ጥጋብ ለልቤ የቅርቤ
የጸሎቴ ምላሽ ሁሌ አለህ አጠገቤ
እራሴን ሳይ ገረመኝ ዛሬ እረጋ ብዬ
ለካስ ኢየሱሴ ነህ ያለኸው በላዬ
ኢየሱስ የእኔ ሰላሜ…..
እኛ እናውቅሃለን ስትረዳን ስላየን
እኛ እናውቅሃለን ስራህን ስላየን
እኛ እናውቅሃለን ክንድህን ስላየን
እኛ እናውቅሃለን ሀይልህን ስላየን
ጌታ ድንቅ ነህ አቻ የሌለህ
ኧረ አንተስ ድንቅ ነህ ወደር የሌለህ
ከስንት ውጣውረድ ማለፍ ከማንችለው
አስበን ተጨንቀን ከማንወጣው
በአንተ ተደግፈን አርነት ወጥተናል
ሀይልህን ልናውጅ በፊትህ ቆመናል
ካንተ ምንቆጥበው ምንም ነገር የለን
ልንሰጥህ ወደናል ያለንን አውጥተን
አንተው በሰጠኸን ልሣን ባርከኸን
ለአንተ ለአምላካችን እንዘምራለን
አንተን ታምነን ወጥተን ስንት ድንቅ አየን
እቅዳችን ሰምሮ ልባችን ደስ አለን
እጃችን በአፋችን ጭነን ተገርመናል
በስራህ ልዩ ነህ ግሩም ነህ ብለናል
ከገመትነው በላይ ሆነብን ውለታህ
አውርተነው አያልቅም ያንተን መልካም ስራ
እየተገረምን አለን እንኖራለን
ስለአንተ መግለጫ ሚመጥን ቃል አጥተን
ወንጌሉን ንገሩ በጨለማ ለሚኖሩ
ኢየሱስ ያድናል ያበራል ብርሃን በሉ
ወንጌሉን አብስሩ በጨለማ ለሚኖሩ
ኢየሱስ ያድናል ያበራል ብርሃን በሉ
1. አላያችሁም ወይ እውራን ሲበሩ
የእግዚአብሔር አብ እጆች ታሪክን ሲሰሩ
ነፍሱ ለደረቀ ዛሬ የሚያረካ ውሃ
ከወንጌሉ ይፈልል ስበኩ ይህን ቃል
2. ባደባባይ ውጡ ቃሉን አብሩ ዝሩ
በመንገዳችሁም ጌታን አስቀድሙ
ሰራተኛው ጥቂት መከሩ ብዙ ነው
የምስራቹን ቃል ቶሎ እናብስረው
3. የወንጌሉን አደራ ታላቅ ነው እወቁ
ቢመችም ባይመች የሱስን ስበኩ
ያላመኑ ይስሙ ይዩ ይህን ብርሃን
ሲኦል ባዶ ትቅር ሁሉም በእርሱ ይዳን
4. አክሊላችን የሱስ ዛሬም ያከበርነው
በእግዚአብሔር አብ ቆሞ ምስክራችን ነው
በማዕዱም ግብዣ ያገለግለናል
እስከዘለዓለም ያም እረፍት ይሆናል
ዓይኔ እንዳላየ ጆሮዬ እንዳልሰማ /2/
እንዴት እንዴት ልሁን እኔ አልችልም
አፌም ለውለታህ ዝም አይልም /2/
ዕለት በዕለት ድንቅ እያሳየኝ
ጌታ አድራጎትህ ስላስገረመኝ
ደግሞ ላውራ እንጂ ለመጪው ትውልድ
እንዴት መልሼ ይሄን ልካድ /2/
አንዴም አላውቅም ርቄ ከቤትህ
ከድንቁ ሥራ ከታምራትህ
አምኖ ዓይኔ አይቶ ጆሮዬም ሰምቶ
አልችልም መኖር ይህን እረስቶ ይህን ዘንግቶ
ማውራት አንዳይችል ነፍስ እንደሌለው
እንደቁም ባሕር ዝም እንደሚለው
ይቅርብኝ እኔስ እንዲህ መኖር
አብቅቶኝ የሱስ ለቁም ነገር ለዚህ ክብር
ያልነበርኩትን ዛሬ ሆኛለሁ
አዲስ ነው ስሜ አዲስ ሆኛለሁ
ባንተ ነው የሱስ ይህ የሆነልኝ
ሁሉም እውነት ነው ምስክርህ ነኝ /2/
የሚረዳኝ የሚያግዘኝ የለምና ከእኔ አትራቅ
የደስታዬ የሰላሜ ምንጭ እኮ ነህ ያዝ እጄን አትልቀቅ /2
ብቸኝነት ህይወቴን ሲከባት
ሲያናውጣት እጅግ ሲፈትናት
አቅሜ አይችልም ይከብደኛል ለኔ
ቶሎ ናልኝ ቶሎ ና መድህኔ
ደስ አይለኝም አንተ የሌለህበት
በመንፈስህ ያልተገኘህበት
ከጎኔ ሁንልኝ ረዥም ነው የኔ መንገድ
ካንተ ሌላ እኔ የለኝም ዘመድ
እኔ አልሻም እኔን የሚረዳ
የተነሳ ከደምና ስጋ
አንተ ሁነኝ ምርኩዜ እረዳቴ
ኢየሱሴ ይሄ ነው መሻቴ
የሰማይ የምድር ንጉስ
መንግስትህ የማይፈርስ
አንተ ነህ ኢየሱስ /2/
ያገር ገዢዎች ራስ
የንጉሶች ንጉስ
አንተ ነህ እየሱስ
ንጉስ ነገስታት
ላመኑብህ ሕይወት
ኢየሱስ ነህ በእውነት
መንግስትህ በጣም ይስፋ
የሰው ነፍስ እንዳይጠፋ
ክርስቶስ የኛ ተሰፋ
በቁርባን ስውር ነህ
በሐይማኖት ላየህ
ኢየሱስ ሆይ ውብ ነህ
ስወድህ ውደደኝ
ስጠራህ ቅረበኝ
ያላንተ ማን አለኝ
በፍቅርህ ተመርቼ
በሐይማኖት ፀንቼ
እንዳገኘህ በርትቼ
ከፍቅርህ አልፋቅ
ከልብህ አልራቅ
አንተን ብቻ ልወቅ
ይሆናል በእርሱ ይሆናል
ይሳካል በእግዚአብሔር ይሳካል
ዛሬ ያስጨነቀ ያሳሰበኝ
ቀን አለው በእርሱ ይከናወናል
1.ለሃሳብ ለጭንቀት አልሰጥም ኡኡታ
ይልቅ ለእግዚአብሔር ነግርኩት ለጌታ
ሁሉንም ሰጥቼ ለእርሱ አልከበደው
አከናወነልን ሸክሜን አቃለለው
2.ተውኩለት ለጌታ እርሱ ያውቅበታል
ለኔ ሚጠቅመኝን ሚበጀኝን ያውቃል
ነገርኩት ሁሉንም በመልኩ ሰራልን
ያስጨነቀን ጠፋ አደላደለልኝ
3.ልቤ ቢዝልብን ጉልበቴ ቢከዳኝ
ቢጋርድም አይኔ ጨለማ ቢውጠኝ
አልገደበኝ ድቅድቅ ለጌታ ለመንገር
የጭንቀቱን ገመድ በደሙ ለማሰር
4.የምን ለቅሶ ሀዘን የኛ ጌታ አለ
ሀያሉ አባታችን ከኛ ዞር አላለ
ሮጠን መጠጊያችን እሱ አለኝታችን
የጭንቃችን ድራሽ አጋር ጓደኛችን
ይሆናል በእርሱ ይሆናል
ይሳካል በእግዚአብሔር ይሳካል
ዛሬ ያስጨነቀ ያሳሰበኝ
ቀን አለው በእርሱ ይከናወናል
1.ለሃሳብ ለጭንቀት አልሰጥም ኡኡታ
ይልቅ ለእግዚአብሔር ነግርኩት ለጌታ
ሁሉንም ሰጥቼ ለእርሱ አልከበደው
አከናወነልን ሸክሜን አቃለለው
2.ተውኩለት ለጌታ እርሱ ያውቅበታል
ለኔ ሚጠቅመኝን ሚበጀኝን ያውቃል
ነገርኩት ሁሉንም በመልኩ ሰራልን
ያስጨነቀን ጠፋ አደላደለልኝ
3.ልቤ ቢዝልብን ጉልበቴ ቢከዳኝ
ቢጋርድም አይኔ ጨለማ ቢውጠኝ
አልገደበኝ ድቅድቅ ለጌታ ለመንገር
የጭንቀቱን ገመድ በደሙ ለማሰር
4.የምን ለቅሶ ሀዘን የኛ ጌታ አለ
ሀያሉ አባታችን ከኛ ዞር አላለ
ሮጠን መጠጊያችን እሱ አለኝታችን
የጭንቃችን ድራሽ አጋር ጓደኛችን